ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

ዲ.ዩ፤ ጥር 1/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ጥር 01/2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ተገኝተዋል ያላቸውን አምስት መምህራን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት (Associate professor) ማዕረግ አካዳሚክ ደረጃ ዕድገት (promotion) ሰጥቷል።

Read more

ለሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች በቡና ጥራት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ዲ.ዩ፤ ጥር 1/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ከኢትዮጵያ ሴቶች ቡና አልሚ ገበሬዎች ማህበር (Women in coffee Ethiopia ) ጋር በመተባበር በቡና ምርት ዙሪያ ለሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

Read more

የመቻቻልና የአብሮነት ቀንን አስመልክቶ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተካሄደ፤

ዲ.ዩ፣ ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ)፣ የመቻቻልና የአብሮነት ቀንን ምክኒያት በማድረግ በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን የተመራ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ሁለገብ ስታዲየም ተከናውኗል።

Read more

በኬሚስትሪ “ቨርቹዋል”ቤተ-ሙከራ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ዲ.ዩ፤ ታሕሳስ 19/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የኬሚስትሪ መምህራን በኬሚስትሪ ቨርቹዋል ቤተ ሙከራ ዙርያ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

Read more

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተልዕኮ ልየታውን (Differentiation) መሰረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ተገለጸ

ዲ.ዩ፤ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተልዕኮ ልየታውን መሰረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ የተገለጸው የተልዕኮ ልየታ ትግበራ ስትራቴጂው ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ቀርቦ በተገመገመበት ወቅት ነው።

Read more

ነጻ የሕግ አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤

ዲ.ዩ፤ ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ.)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ት/ቤት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ጋር በመተባበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ ነጻ የሕግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሚሰሩ የሕግ ባለሙያዎች እና በሕግ ት/ቤት ለሚማሩ የሕግ ተማሪዎች በመሬት ሕግ፣ በውርስ ሕግ፣ በቤተሰብ ሕግና በፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ ላይ ለሦስት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Read more

ተማሪዎችን በተለያየ መልኩ ማገዝ የሚችል ‘Chat bot’ መሰራቱ ተገለጸ

ዲ.ዩ፤ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርማቲክስ ት/ቤት በቴክኖሎጂ ዙሪያ ሴሚናር ባዘጋጀበት ወቅት በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ተሰርቶ የቀረበው ተማሪዎችን ሊያግዝ የሚችል “Virtual Assitance (chatbot )” በትምህርት ክፍሉ እውቅናን አግኝቷል።

Read more