በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ
ዲ.ዩ፦ መስከረም 26/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ እና ከጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር “የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የንባብ ሳምንት አካል የሆነው የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስ እና ሥነ -ሰብዕ ኮሌጅ አስተባባሪነት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል ።