ዲላ ዩኒቨርሲቲ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአራቱም ግቢዎች ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል፡፡

ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል እንደ ሀገር እቅድ ተይዞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በአራቱም ግቢዎች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራ ማከናዎናቸውን ገልጸዋል።

Read more

የልዩ የክረምት ስልጠና ተሳታፊ መምህራንና ርዕሰ መምህራን ስልጠና ተጠናቀቀ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና አመራሮች የማጠቃለያ ፈተና ተሰጥቶ ስልጠናው ተጠናቋል።

Read more

በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጤና ምርመራ እና ህክምና እየተሰጠ ነው

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 10-20/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት በዲላ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች እየሰጠ ይገኛል።

Read more

የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለክረምት ሰልጣኝ ባለሙያዎች ገለፃና አቀባበል አደረገ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ከ ጂ አይ ዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር ላዘጋጀው የአራተኛ ዙር የግብርና ባለሙያዎች የክረምት ስልጠና ሰልጣኞች አቀባበልና ገለጻ አድርጓል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዋና ዳሬክተር አለሙ ደሳ (ዶ/ር)፤ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፤ አባቶቻችን ቡናን በማምረት የታወቁ ቢሆኑም ምርቱና ውጤቱ ከድካማቸው ጋር የሚጣጣም እንዳልነበር ጠቅሰው ይህ ደግሞ ዘርፉ በዕውቀት ባለመመራቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

Read more

የአግሮ ቢዝነስ ሐሳብ ውድድር ተካሄደ

ዲ.ዩ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ቴክኖሌጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የአግሮ ቢዝነስ ውድድር /Agro-business idea computation/ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማለፍ ውድድር ተካሂዷል።

Read more

ከቅጥር እስከ ጡረታ በታማኝነት

ዲዩ፦ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተቆረቆረበት ጀምሮ በመስራችነት ከተቀጠሩ ጥቂት መምህራን ውስጥ አንዱ ሆኑት መምህር ተሰማ አያሌው ብዙዎች እንደሚሉት- ተሴ ከቅጥር እስከ ጡረታ በታማኝነት አገልግለዋል።

Read more