ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ ዲላ ከተማ ሲገቡ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ጨምሮ፣ የዞኑ ካቢኔ አባላት እንዲሁም የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read more

የላቀ_አስተዋጽኦ_የምስክር_ወረቀት

ዲ.ዩ፦ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ 2016 የትምህርት ዘመን በበይነ-መረብ እና በወረቀት የተሰጠው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጀ ማጠናቀቂያ ፈተና በተሰካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና አስተዋጽዖ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት።

Read more

በምርምር የበለጸገ የአፕል ችግኝ ለአርሶ አደሮች ተሰራጨ

ዲ.ዩ ነሐሴ 20/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከቡሌና ራጴ ወረዳ ለተወጣጡ አርሶ አደሮች በምርምር የበለፀገ የአኘል ችግኝ ስርጭት አካሂዷል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ ዩኒቨርሲቲው በደጋ ፍራፍሬ ዙሪያ በሰፊው እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በዋናነት በአኘል ላይ ለረጅም ጊዜ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ከቡሌ ወረዳ 8 ቀበሌዎች ከራጴ ወረዳ በተመሳሳይ 8 ቀበሌዎች ለተወጣጡ አርሶ አደሮች የአኘል ችግኝ መሰራጨቱን ተናግረዋል።

Read more

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምር ስልጠና ተቋም ሰልጣኞች የመስክ ስልጠናና ልምድ ልውውጥ አካሄዱ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 19/12/16 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምር ስልጠና ተቋም በአራተኛ ዙር እያሰለጠናቸው ያሉትን የግብርና ባለሙያዎች በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ሲማሩ የቆዩትን በተግባር የመስክ ምልከታና ልምምድ እንዲያገኙ ማድረጉ ተገልጿል።

Read more

የኢትዮጵያ ግብርና ናሙና ቆጠራ ስልጠና የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሄደ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 18/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር የተዘጋጀው “የግብርና ቆጠራ ለመረጃ ምሉዕነት” በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ግብርና ናሙና ቆጠራ ባለሙያዎች ስልጠና የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

Read more