የገበያ ጥናት አሰራርን በተመለከተ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ም)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ለአባያ ወረዳ እና ለሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች በገበያ ጥናት መረጃ አሰባሰብ፣ ትንተናና ስርጭት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል።