Dilla University

News

8th International Conference on Mathematics and Mathematics Education

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 09/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት ከጌዴኦ ዞን፣ ከምዕራብ ጉጂ አባያ ወረዳ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ ለተወጣጡ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች በሀገር በቀል ዕውቀት ዙሪያ ሰልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ደርቤ ጅኖ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን በርካታ ሀገር በቀል እውቀቶች ባለቤት በመሆኗ እነዚህን አገር በቀል እውቀቶች ጠብቀን ማቆየት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ደርቤ አክለውም፤ የማህበረሰቡ የተለያዩ እሴቶችና ልዩ ልዩ ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ በማስተላለፍ ትውልድ እንዲማርበት ታስቦ የተዘጋጀው ስልጠና መሆኑን አንስተዋል። ከስልጠናው በኋላ ለቅርሶች ያለንን ግንዛቤን በመጨመር ለትውልድ እውቀታችሁን ማሸጋገር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ባህልና ቅርስን አስጠብቆ ማቆየት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ አሁን ላይ ያሉ ቅርሶችን የማስጠበቅ ስራ ከሚፈጥረው ከኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት አንጻርም መታየት እንደሚገባው አሳስበዋል።
ማህበረሰቡ በአካባቢው የሚገኙ ባህልና ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ ብሎም ለትውልድ እንዲተላለፍ መስራት ይገባል ሲሉ አቶ ተካልኝ አያይዘው ተናግረዋል።
ስልጠናውን ከሰጡት መካከል ዶ/ር አብዮት መብራቴ፣ የዲላ ዩኒቨርሲት የሀገረሰብ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር፤ ለራሳችን ቅርሶችና ባህል ያለን አመለካከት እንዲያድግ በማድረግ የሚኖረውን የውጭ ባህል በባህላችን እና በቅርሶቻችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር መስራት እንደሚገባ መክረዋል።
ስልጠናውን ሲከታተሉ ያገኘናቸው ሰልጣኞች በቂ እውቀትና ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸው ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢው ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et