August 31, 2024Top News የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምር ስልጠና ተቋም ሰልጣኞች የመስክ ስልጠናና ልምድ ልውውጥ አካሄዱ ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 19/12/16 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምር ስልጠና ተቋም በአራተኛ ዙር እያሰለጠናቸው ያሉትን የግብርና ባለሙያዎች በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ሲማሩ የቆዩትን በተግባር የመስክ ምልከታና ልምምድ እንዲያገኙ ማድረጉ ተገልጿል። Read more
August 31, 2024Top News የኢትዮጵያ ግብርና ናሙና ቆጠራ ስልጠና የመክፈቻ ስነ ስርዓት ተካሄደ ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 18/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር የተዘጋጀው “የግብርና ቆጠራ ለመረጃ ምሉዕነት” በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ግብርና ናሙና ቆጠራ ባለሙያዎች ስልጠና የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። Read more
August 31, 2024Top News ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ ማስታወቂያ፡ ዲላ ዩኒቨርሲቲ #በዲላ፣ #በይርጋጨፌ፣ #በሀዋሳ እና #ሻሸመኔ ማዕከላት በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት (Weekend) መርሃግብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች Read more
August 31, 2024Prime News, Top News ዲላ ዩኒቨርሲቲ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአራቱም ግቢዎች ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል፡፡ ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል እንደ ሀገር እቅድ ተይዞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በአራቱም ግቢዎች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራ ማከናዎናቸውን ገልጸዋል። Read more
August 31, 2024Top News የልዩ የክረምት ስልጠና ተሳታፊ መምህራንና ርዕሰ መምህራን ስልጠና ተጠናቀቀ ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 15/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና አመራሮች የማጠቃለያ ፈተና ተሰጥቶ ስልጠናው ተጠናቋል። Read more
August 31, 2024Prime News, Top News የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ ዲ.ዩ. ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ነሐሴ11/2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። Read more
August 31, 2024Top News በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጤና ምርመራ እና ህክምና እየተሰጠ ነው ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 10-20/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት በዲላ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች እየሰጠ ይገኛል። Read more
August 31, 2024Top News የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለክረምት ሰልጣኝ ባለሙያዎች ገለፃና አቀባበል አደረገ ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ከ ጂ አይ ዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር ላዘጋጀው የአራተኛ ዙር የግብርና ባለሙያዎች የክረምት ስልጠና ሰልጣኞች አቀባበልና ገለጻ አድርጓል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዋና ዳሬክተር አለሙ ደሳ (ዶ/ር)፤ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፤ አባቶቻችን ቡናን በማምረት የታወቁ ቢሆኑም ምርቱና ውጤቱ ከድካማቸው ጋር የሚጣጣም እንዳልነበር ጠቅሰው ይህ ደግሞ ዘርፉ በዕውቀት ባለመመራቱ እንደሆነ ገልጸዋል። Read more
August 31, 2024Top News የአግሮ ቢዝነስ ሐሳብ ውድድር ተካሄደ ዲ.ዩ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ቴክኖሌጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የአግሮ ቢዝነስ ውድድር /Agro-business idea computation/ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማለፍ ውድድር ተካሂዷል። Read more
August 8, 2024Top News ከቅጥር እስከ ጡረታ በታማኝነት ዲዩ፦ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተቆረቆረበት ጀምሮ በመስራችነት ከተቀጠሩ ጥቂት መምህራን ውስጥ አንዱ ሆኑት መምህር ተሰማ አያሌው ብዙዎች እንደሚሉት- ተሴ ከቅጥር እስከ ጡረታ በታማኝነት አገልግለዋል። Read more