Dilla University

News

8th International Conference on Mathematics and Mathematics Education

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

Green University, Sustainable Future

Prime News Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 03/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የስፔኑ የካታሎኒያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ልማት በስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘሬዝዳንት፤ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ዘርፍ ጋቫ የስፖርት ልማት በጋራ ለመስራት ዛሬ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በአይነቱ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ አክለው፤ የዚህ አይነቱ ስምምነት በስፖርት ዘርፍ የተገኘ ትልቅ እድል መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን ያመቻቹትን የኢትዮ ጋቫ ተወካይን እንዲሁም የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራንን አመስግነዋል።
ማስረሻ ኢራጎ (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና የዚህ ስምምነት አስተባባሪ፤ በበኩላቸው ባለፉት ግዜያት የስፓርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ለአካባቢው ድጋፍ በማድረግ በርካታ ወጣቶችን ማፍራቱን ተናግረዋል።
ዶ/ር ማስረሻ አያይዘውም፤ ስፔን በስፓርቱ ዘርፍ የተሻሉ ባለሙያዎች ያሏት ሀገር በመሆኗ ከዚህ ስምምነት ከፍተኛ የሙያ ድጋፍ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በክለብ ለታቀፉ ወጣቶች ሙሉ ትጥቅ ለማበርከት ቃል እንደተገባ አስረድተዋል። በቀጣይ ባለሙያዎችን ወደ ሀገራቸው ወስደው ለማሰልጠን ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑንም ተናግረዋል።
የስፔን ካታሎኒያን ግዛት ጋቫ የስፓርት ልማት ኘሬዝዳንት ራብላ ፖምፒዮ (Mr. Rbla Pompeu Fabra)፤ በኢትዮጵያ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸው፤ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
አያይዘውም፤ በአውሮፓ እስታዳርድ ትጥቅ በማሟለላት ብቁ ዜጋ ለማፍራት አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
አሰልጣኝ ይብራ ማሀር፣ የዲላ ዶንቦስኮ እና ሰላም ሆስፒታል የእግር ኳስ አሰልጣኝ፤ አሁን ላይ ወጣቱ ለስፖርት ያለው ትኩረት እለት ተዕለት እየጨመረ በመሆኑ የዚህ አይነቱ ድጋፍና ክትትል መደረጉ የተሻለ ወጣት ስፖርተኛ ማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል።