በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጤና ምርመራ እና ህክምና እየተሰጠ ነው

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 10-20/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት በዲላ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች እየሰጠ ይገኛል።

Read more

የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለክረምት ሰልጣኝ ባለሙያዎች ገለፃና አቀባበል አደረገ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ከ ጂ አይ ዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር ላዘጋጀው የአራተኛ ዙር የግብርና ባለሙያዎች የክረምት ስልጠና ሰልጣኞች አቀባበልና ገለጻ አድርጓል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዋና ዳሬክተር አለሙ ደሳ (ዶ/ር)፤ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፤ አባቶቻችን ቡናን በማምረት የታወቁ ቢሆኑም ምርቱና ውጤቱ ከድካማቸው ጋር የሚጣጣም እንዳልነበር ጠቅሰው ይህ ደግሞ ዘርፉ በዕውቀት ባለመመራቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

Read more

የአግሮ ቢዝነስ ሐሳብ ውድድር ተካሄደ

ዲ.ዩ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ቴክኖሌጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የአግሮ ቢዝነስ ውድድር /Agro-business idea computation/ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማለፍ ውድድር ተካሂዷል።

Read more