ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) በመላው ዓለም እየተከበረ ነው

ዲ.ዩ፦ የካቲት 29/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ እንዲሁም በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ለ47ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለምአቀፍ የሴቶት ቀን አስመልክቶ ተከታዩን መልዕክት ያስተላልፋል።

ለድህረ-ምረቃ አዲስ አመልካች ተማሪዎች

የድህረ-ምረቃ ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ሐሙስ፣ የካቲት 30/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ መሆኑን እየገለፅን አመልካቾች ለፈተና መቀመጥ መቻላችሁን ለመማር ካመለከታችሁበት የትምህርት ክፍል ጋር በመነጋገር በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ፈተናውን እንድትፈተኑ እናሳውቃለን።
ሬጂስትራር እና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት
...................
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የአንደኛ አመት የጋራ ኮርሳቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ለመምረጥ የሚረዳ ገለፃ ተሰጠ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 24/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና፣ ሐሴዴላ እና ኦዳያአ ግቢዎች የጋራ ኮርስ (Common Courses) ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍሎችን መርጠው ለመቀላቀል የሚያስችል ገለጻ ተሰጥቷል።
በዩኒቨርሲቲው የፍሬሽማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዲን የሆኑት አስናቀ ይማም (ዶ/ር ) እንደተናገሩት ገለፃው ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የተዘጋጀ ነው።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 22/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ተወስኖ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል። ይህን የመውጫ ፈተና ለማከናወን የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሁኔታዎችን አስመልክቶ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ መንግስት እንደ ሀገር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመስጠት የተቋማቱ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ምልከታ ለማድረግ የተለያዩ ቡድኖች መሰየማቸው ተገልጿል።

ማስታወቂያ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ "በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና የአስተዳደር ኃላፊዎች ምርጫ እና ምደባ ለመደንገግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 002/2011" መሰረት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በውስጥ ማስታወቂያ አወዳድሮ መሰየም ይፈልጋል።
ስለሆነም አመልካቾች የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸውን እንዲሁም ዋና ተግባሩን ለማሳደግ የሚረዳ አጭር ሀሳብ (Brief Proposal) በማዘጋጀት እና በማሸግ ከየካቲት 20/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 04/2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
አወዳዳሪ ኮሚቴ

በተቋማዊ የለውጥ ስራ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍሎችና ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 18/2015 ዓም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል 'SBFR' (System Bottleneck Focused Reform) ተቋማዊ የለውጥ ስራ መተግበር ከጀምረ ወዲህ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍሎችና ሰራተኞች እውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር አካሂዷል።
ዶ/ር ምፅዋ ሩፎ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ም/ኘሬዝዳንት፤
ላለፉት 13 ሳምንታት በጤና ሚኒስቴር እየተተገበረ ያለውን 'ሪፎርም' እንደተቋም ተቀብለን መተግበር ከጀመርን ጀምሮ ትልቅ ለውጥ ታይቷል ብለዋል።
በሀገሪቱ 'ሪፎርሙ' ከተተገበረባቸው 36 ሆስፒታሎች መካከል የዲላ ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘቱን አያይዘው ተናግረዋል ዶ/ር ምፅዋ።

ለአቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች ቤት የማደስ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 14/2015 ዓም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት አባላት በይርጋጨፌና ወናጎ ወረዳዎች ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የቤት የማደስ በጎ ፍቃድ አገልግሎት አስጀመሩ።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ባለፉት አመታት በዲላ እና ወናጎ አካባቢ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና የተወሰኑ ለቤት ቁሳቁስ የሚሆኑ እቃዎችን በልዩ ሁኔታ የመደገፍ ስራ ተሰርቶ ነበር ብለዋል። በዘንድሮው አመትም ይህንኑ መሰል በጎ ፍቃድ አገልግሎት በይርጋጨፌ እና ወናጎ ወረዳዎች ለማከናወን ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው እየሰራ ያለው ስራ ለአከባቢው ባለሀብት እና አስተዳደር አነሳሽ በመሆኑ እንደዚህ አይነት የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመርዳት መትጋትና መቀናጀት እንደሚገባም ዶ/ር ችሮታው አሳስበዋል።

Pages