የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ስራ አስኪያጅ ደራሲ የዝና ወርቁ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራን እና ተማሪዎች ጋር ተወያዩ ዲ.ዩ፦ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ስራ አስኪያጅ ደራሲ የዝና ወርቁ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራን እና ተማሪዎች ጋር ትምህርታዊ ውይይት አካሄዱ። ደራሲ የዝና ወርቁ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ዘመናዊ አጭር ልቦለድ ደራሲ ሲሆኑ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ እና በልዩ ልዩ ጋዜጦች ዋና አዘጋጅ ሆነውም ሰርተዋል።
"በዩኒቨርሲቲያችን የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመስጠት ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው" ማቴዎስ ሀብቴ (ዶ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ ዲ.ዩ፦ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ከያዝነው 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደውን የመውጫ ፈተና (Exit exam) ዲላ ዩኒቨርስቲ ለተመራቂ ተማሪዎቹ በ"ኦንላይን" ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ዓለማቀፉ የሴቶች ቀን "ማርች 8"ን ተንተርሶ በ"እናት" መፅሐፍ ላይ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ ዲ.ዩ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርስቲ "ማርች 8" የሴቶች ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ “ፈጠራና ቴክኖሎጂ ለጾታ እኩልነት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል። በእለቱም ጭብጡን ሴትነትን ከቤተሰብ ህይወት እስከ ማህበረሰባዊ ሁለንተናዊ ጉዳዮች በይኖ የሚዳስስ "እናት" የተሰኘ መፅሐፍ ተመርቆ ለውይይት ቀርቧል። መፅሐፉን በዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ይሁኔ አየለ ናቸው የፃፉት።
በጣሊያን ቱሪን ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ ዲ.ዩ፦ መጋቢት 06/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በተማሪዎች የልውውጥ ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር ቱሪን ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሀገሪቱ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። በቱሪን ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ወራት ልምድ ለመለዋወጥ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የሄዱት ስድስቱ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በቱሪን ከተማ በሚገኘው በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ፅ/ቤት ነው ውይይቱን ያደረጉት።
በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ወስዳችሁ፣ በአቅም ማሻሻያ (remedial) ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበት ቀን ከመጋቢት 14-15/2015 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን።
ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ዲ.ዩ፦ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት ልማት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬትና ተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን ለበላይ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ዲኖች እና ቡድን መሪዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር (Trasnformational Leadership) ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል።