

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሚኖራቸው ሚና የላቀ በመሆኑ ምሁራን ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።
..............
ዲ.ዩ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም(ህ.ግ) የሳይንስ ሳምንት አካል በሆነው በፓናል ውይይት ላይ የተገኙ እንግዶችንና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገ/ምክትል ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ ይህ ወቅት መንግስት ለመንግስት ከሚያደርገው ዲፕሎማሲ ባሻገር ወደ ህዝብ ዲፕሎማሲ የተሻጋገርንበት ጊዜ በመሆኑ የህዝብ ዲፕሎማሲ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ይሁን እንጂ የህዝብ ዲፕሎማሲ ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር በጥንቃቄና በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ለአፍራሽ ተልዕኮ ሊውል እንደሚችል መገንዘብ እንዳለብን ተናግረዋል።
የዚህ ዓይነቱ የውይይት መድረክ ባለፉት ግዜያት ለማካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረ የገለፁት ዶክተር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉበትን አከባቢ ማህበረሰብ በምርምር በመደገፍ የማህበረሰብን ህይወት መቀየር ዋና መሪሃቸው መሆኑን ገልፀው እስካሁን በዞናችን ዘመናዊ የምርምር ውጤቶችን ከማዳረስ አኳያ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በማቀድ የማህበረሰብን የልማት ፍላጎት ጥያቄ ለመመለሰ ከባለፈው ስራችን በበለጠ ለመሰራት ይህ መድረክ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለዞናችን ትልቁ ተቋማችን ነው ያሉን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸው እሰካሁን የተሰሩት ስራዎች በርካታ ቢሆኑም አብሮ ተያይዞና አቅዶ የመስራት ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
Public and International Relations Directorate
P.O.Box: 419
E-mail: pirdir@du.edu.et
Phone: +251461310001
: +251463312459
Dilla University
University of the Green Land!
The website Developed by DUICT Business App Dev't