የሀገር በቀል እውቀት ቅድመ ማስጠንቀቂያ የምርምር ማረጋገጫ ወርክ ሾኘ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ::

ዲ ዩ ሐምሌ 10/2013 (ህ.ግ) አለም ከተፈጠረች አንስቶ አባቶቻችን የባህላዊ እውቀትን ጠብቀው አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ ማቆየታቸውን የገለፁልን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ተወካይና የአስ/ተማ/አገልግሎት ም/ኘሬዚዳንት ዶ/ር ዲዊት ሀዬሶ በአለማችን በርካታ ችግሮች ስከሰቱ በምድር ያለውን ምርምር አልፈው በህዋ ስመራመሩ የቆዩት ዛሬ ላይ ለሀገር በቀል ባህላዊ እውቀት ትልቅ እውቅና በመስጠት ላይ ናቸው ብለውናል::
አክለውም ዶ/ር ዳዊት አሁን ላይ የምታየው ስልጣኔ መነሻው ባህላዊ እውቀት በመሆኑ ሁለቱንም በማቀናጀት የህዝቡን ኑሮ ማሻሻልና ጤናን መጠበቅ ይገባል ብለዋል::

የዩኒቨርሲቲው ካውንስል የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የ800,000 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ዲ/ዩ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) በዩኒቨርሲቲው ካውንስል የተደረገው የ800,000 ብር ድጋፍ ሴት ተማሪዎችን ውጤታማ እና ስኬታማ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ እንደሆነ የገለፁት የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለም ብርሃኑ ይህ ድጋፍ ለንጽህና መጠበቂያ እና ለመማሪያ ቁሳቁስ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ አለም አያይዘውም የዚህን መሰል ድጋፍ ባለፉት ጊዜያትም የዩኒቨርሲቲው ካውንስል እያደረገ እንደመጣ ገልፀው ድጋፉ የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎችን በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ ተማሪዎቹ በተቋሙ ላይ ያላቸውን እምነትና አጋርነት የሚጨምር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Day-3 Heart Convention, 2021, MoSHE

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው "ወደ ዕውቀት-መር ኢኮኖሚ" በሚል መሪ ቃል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው HEART Convention 2021 በዛሬው ውሎ በዋናነት በድጅታል ስትራቴጂ እና በኢንዱስትሪ ሊንኬጅ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል::
የምርምር÷ የፈጠራና የጉድኝት ስራዎችን ለማበረታታት ታስቦ በተዘጋጀው በዚህ ኮንቬንሽን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች÷ የቴክኒክና ሙያ እና የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ተቋማት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን ዲላ ዩኒቨርሲቲም በምርምር÷ በፈጠራ እና በኢንዱስትሪ ግንኙነት ስራዎች የተከናወኑትን ተግባራት ለታዳምያን እያቀረበ ይገኛል::
 
ሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓ.ም.
ኢንተርኮንትነንታል ሆቴል, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

ማስታወቂያ: በዳግም ምደባ አዲስ ለተመደባችሁ ፍሬሽማን ተማሪዎች በሙሉ

በሳይንስና ከፍተኛ ት/ሚኒስቴር አማካኝነት በዳግም ምደባ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ አመት ተማሪዎች የምዝገባ ቀን እስከ ዐ9/11/13 ዓ/ም ድረስ ብቻ መሆኑን እየገለጽን በተጠቀሱት ቀናት ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃችሁን እና ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋናው ግቢ እና በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በኦዳያአ ግቢ ባሉ የሬጅስትራርና አሉምናይ ዳ/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡
ማሳሰብያ፡- ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ ለምዝገባ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቡና ልማት ላይ ስልጠና ለመስጠት ለግብርና ባለሙያዎች አቀባበል አደረገ፡፡

ዲዩ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከኢሊባቡር ዞን ለተወጣጡ 39 የግብርና ባለሙያዎች በቡና ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና ለመስጠት ለሰልጣኞች አቀባበል አድርጓል፡፡
በአቀባበሉ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በምርምር ላይ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን በአርሶአደሩ ዙሪያ መልካም ልምዶችን ለማስፋትና የቡና ሴክተሩ ራሱን ችሎ በተሻለ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ይህን መሰል ስልጠና መሰጠቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች በካምፓስ ሕይወት አኗኗር ጥበብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ::

ዲ ዩ ሐምሌ 3/2013(ህ.ግ.) ወደ ዩኒቨርስቲያችን ተመድበው የመጡትን ተማሪዎች ተቋሙም ሆነ ክፍሎች ለመቀበል ያደረጉትን ዝግጅት በመግለፅ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኤች አይ ቪ መ/መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ሽፈራዉ ወደ መማር ማስተማር ስራ ከመገባቱ በፊት የካምፓስ ህይወት የመምራትን ጥበብ ግንዛቤ እየተዝናኑ እውቀት እንዲቀስሙ ታሰቦ የተዘጋጀ መደረክ ነው ብለዋል::
በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ግንዛቤ ካስጨበጡት መካከል በካውስልንግ የረዥም አመታት ልምድ ያላቸው የስነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር ታረቀኝ ታደሰ ተማሪዎች በተቋም ቆይታቸው ወቅት እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን ከሕይወት ተሞክሮአቸውም አካፍለዋል::

ለ2013 አዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ዲ/ዩ ሐምሌ 2/2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት የፍሬሽማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዲን ዶ/ር አስናቀ ይማም ዲላ ዩኒቨርሲቲ እናንተን ለመቀበል ማናቸውንም ዝግጅት አጠናቆ የቆየ በመሆኑ በቆይታችሁ የሰመረ ጊዜ ይኖራችኋል ብለዋል፡፡

ማስታወቂያ :ለዲላ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በሙሉ

"የጠራ የሳይንስና ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራሞች እና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕድገት፣ልማትና ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ፣ እና በቁልፍ የውጤት አመላካች ዙሪያና በዲላ ዩኒቨርስቲ የዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ለመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የተዘጋጀ ሥልጠና ከመጋቢት 13-14 ዓ.ም ድረስ በሦስቱም ግቢዎች ይሰጣል። በመሆኑም በዕለቱ በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ፣ በኦዳያኣ ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽና በሆስፒታል ግቢ በዋናው ቤተመጻሕፍት የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ ባለመቅረት እንዲገኝ እናሳስባለን።

Pages