የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሁለተኛ ቀን የመስክ ምልከታ ዛሬም ተካሂዷል

ዲ.ዩ፦ ግንቦት 26/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከትላትን ጀምሮ የመስክ ምልከታ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እያካሄዱ እንደሆነ መዘገባችን አይዘነጋም።
በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሬ ሌንጮ (ዶ/ር) የተመራው ቅኝት አድራጊ ቡድን ዛሬ ከሰአት በፊት በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ተመልክቷል።
ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው የከሰአት በፊት ምልከታ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለውን አዲሱን የህክምና እና ማስተማሪያ ሆስፒታል፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማከሚያ ማዕከልን፣ የእፅዋት ጥበቃ እና ኢኮቱሪዝም ማዕከልን፣ እንዲሁም በቀድሞው ዋና ግቢ የሚገኘውን የዶሮ እርባታ ጣቢያን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
ምልከታ በተደረገባቸው የልማት ስራዎች ዙሪያም የሚመለከታቸው በዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ