በሥነ-ምግባር የታነጸ አመራር ከሙስና የፅዳች ኢትዮጲያ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ18 ግዜ በሀገራችን ለ17 ግዜ የፀረ-ሙስና ቀን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ::

ዲ-ዩ -ህዳር 30/2014ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) ሙስና የመንግስት እና የህዝብ ሀብት የግል ወይም የቡድን ፍላጎትን በህግ-ውጥ መንገድ ለግል ጥቅም ለሟሟላትና መልካም ስነ-ምግባር በሌላቸው ሰዎች የሚፈጸም፣ ተግባር፣ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መብራቴ ሽፈራው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር የሙስና መከሰት ዋነኛ መንስኤው የመልካም ስነ-ምግባር እሴቶች መሽርሸር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም ወ/ሮ ማብራቴ መልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲቀጭጭ የአገልግሎት አሰጣጡም ዜጎች በሚፈልጉት ደረጃ አንዳይሰጥ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በ2014 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ የፀረ ሙስና ቀን በምናከብርበት አጋጣሚ ሙስና በመንግስት ሀብትና ንብረት እንዲሁም በሰው ህይወት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከባድ መሆኑን የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ሙስናን ለመከላከል ሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ እንዲነሳሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር ችሮታው በቀጣይ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሙስናን ለመከላከል የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ዜጎችን በራሳቸውና በእያንዳንዱ የትምህርት መስክ ጠንክርው በመማር በራሳቸው የሚተማመኑ ምሩቃንና ሙሁራንን በማፍራት ውጤታማ ስራ መስራት ያስፍልጋል ብለዋል፡፡
የሕግና አስተዳደር ኮሌጅ መምህርና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ፍቅሩ ‹‹በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዶች ኢትዮጲያ›› በሚል ርዕስ የውይይት ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በፓናሉ ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይቶች ተከናውነዋል፡፡
በመጨረሸም የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ቀን በዓልን አስመልክቶ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ለተወዳደሩና አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡