የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ዶ/ር አበባየሁ ታደሴ እና ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አዲስ በተዋቀረው በደብብሕክ መንግስት ምስረታ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሆነው ተሾሙ::

ዛሬ በተዋቀረው በደብብሕክ የመንግስት ምስረታ ላይ የክልሉ አፌ-ጉባኤ እና ምክትል አፌ-ጉባኤ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾሙ የሚታወቅ ሲሆን በርዕሰ መስተዳድሩ የተከበሩ አቶ ርስቱ ይርዳው አቅራብነት የክልሉ ካቢኔ አባላትና የፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች ተሰይመዋል::
ከዕጩዎች መካከል የዩኒቨርሲቲያችን የምርመርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት እና የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር አበባየሁ ታደሴ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና የዩኒቨርሲቲያችን የሀገር በቀል ጥናት ተቋም (Indigenous Institute) ኃላፊ እና የኢዜማ ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ የክልሉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል::
ዩኒቨርሲቲው ለምሁራኑ ሹመት የተሰማውን ላቅ ያለ ደስታ እየገለፀ ለተቋማችን ስላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናውን ያቀርባል::
በተግባር የተፈተሸ ስብዕናቸው ምሁራኑ የተሰጣቸውን ክልላዊና ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ የዩኒቨርሲቲውን መተማመን ከፍ የሚያደርገው ሲሆን መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ይመኛል::