የዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተቀጠሩ የካምፓስ ፖሊስ አባላት ሲሰጥ የቆየው ሙያዊ ስልጠና ተጠናቀቀ::

ዲ.ዩ. ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም. (ህ.ግ.) በሀገራችን ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ተቋማት የሰላም ችግር እንደነበረ የተናገሩት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ኘሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ተወካይ በነዚህ ጊዜያት ተቋማችን ሰላማዊ ሆኖ የቆዬ ሲሆን ይህን ሰላም በቀጣይ እንደምታስቀጥሉ እተማመናለሁ ብለዋል::
በዚህ አጭር ግዜ የአካል ብቃት÷ ወታደራዊ ሰልፍ እና ዲስፕሊን በማሰልጠን ተልቅ እገዛ ያደረጉትን የፌዴራል ፖልሶችን አመሰግነው የዚህ አይነቱ ስልጠና በቀጣይ ለአጠቃላይ አባላቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል::
ስልጠናውን ከወሰዱ አዲስ የዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ፖሊሶች መካከል ያነጋገርናቸው አቶ ሳሙኤል ታደሰ እና ጌጤ ጥበብ በበኩላቸው የፌዴራል ፖሊሶች እና የዩንቨርሲቲው አስተዳደር አካላት አባላቱን ብቁ ለማድረግ ስላሳዩት ትጋት በእጅጉ አመስግነው የወሰድነው ስልጠና ለቀጣይ ስራችን ትልቅ ግብአት ይሆነናል ብለዋል::
.....
ትኩስና ወቅታዊ መረጃ እንዲደርስዎ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይጎብኙ፣
......
ዌብሳይት: www.du.edu.et
ቴሌግራም: https://t.me/dprd9
Dilla University
University of the Green Land!