የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተቀጠሩ የካምፓስ ፖሊስ አባላት ስልጠና ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ. ነሐሴ 25 (2013 ዓ.ም.) (ህ.ግ.) በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ አንጋፋ ተቋማት መካከል አንዱ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ዳዊት ሀይሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተ/አ/ም/ፕረዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ተቋሙ ከ5,500 በላይ የአስተዳደርና አካዳሚክ ሠራተኞች የያዘ÷ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች በተለያዩ በመደበኛና በተከታታይ ፕሮግራሞች እንደሚያስተምር ጠቅሰው በቀጣይ 10 ዓመታት በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት በሀገራችን ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም ለመሆን ራዕይ ነድፎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ይሄን ትልቅ ራዕይ ለማሳካት እናንተ አዲስ የተቀጠራችሁ የካምፓስ ፖሊስ አባላት በትክክለኛ ስነ- ምግባር ጠንክራችሁ በመስራት የበኩላችሁን ጥረት እንዲታደርጉ ይገባል በማለት ዶ/ር ዳዊት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ አድማሱ ለማ የመንግስት ሠራተኞች የምመሩበትና የሚተዳደሩበት መምሪያዎች፣ ደንቦችና አዋጆች እንዲረዱና እንዲያውቁ ለአዲስ ተቀጣሪ ሠራተኞች ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ አድርገዋል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ መብራቴ ሽፈራው በበኩላቸው ሥነ- ምግባር፣ የስነ-ምግባር መሪሆዎች፣ ሙስና መከላከል እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሠልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
በመጨራሻም አቶ ይመኑ ዳካ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ዩኒቨርሲቲያችን ሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ ሰላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው በተቋማችን የሚገኙትን የሰውና የቁስ ሀብታቸንን በንቃት እንድትጠብቁ ስሉ ለአዲስ ተቀጣሪ የካምፓስ ፖሊስ አባላትን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡