የዲላ ዩኒቨርሲቲ የረዳት ፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገት ለመምህራን ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 22/2013 ዓ.ም (ህ.ግ.) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር የጤና ዘርፍ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታልና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት መላኩ ኮሌጁ በመማር ማስተማር፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ እንደምገኝ ገልፀው የመምህራን ልማትን በትኩረት እየሰራን ነው ብለውናል፡፡ 

አክለውም አቶ ጌትነት በ2013 ዓ.ም ለአስር መምህራን በምርምር ህትመት፣ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉዳዮች በኃላፊነትና ባላቸው ብቃት በመማር ማስተማር ስራ አፈፃፀም በመመዘን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የረዳት ፕሮፌሰርነት አካዳሚክ ማዕረግ ደረጃ እድገት ተሰቷል ብለዋል፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!!!