Dilla University

News
Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 14/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦የኪነ ህንፃ ትምህርት ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና እንደሚያስፈትን የተገለጸው የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎችን የመጀመሪያ ዙር ቅድመ መውጫ የሙከራ ፈተና (Mock Exam) ባስፈተነበት ወቅት ነው።
አንተነህ ወጋሶ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን፤ ኮሌጁ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ የኪነ-ህንፃ እና ሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር የቅድመ መውጫ ፈተና መስጠቱን ገልጸዋል።
ከጥር 27-30/2016 ዓ.ም በኢፌድሪ በትምህርት ሚኒስቴር ይሰጣል ተብሎ የታቀደውን የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚፈተኑ የሁለቱ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች አጥጋቢ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው በበለጸገ ዲጂታል የፈተና ስርዓት (I-Exam) የሙከራ ፈተናው መሰጠቱን ዶ/ር አንተነህ አያይዘው ተናግረዋል።
ፈተናው በማዕከል የተዘጋጀውን ብሉፕሪንት መሰረት አድርጎ በተቋሙ መምህራን የተዘጋጀ ሲሆን ተማሪዎች በቀጣይ በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን ሞዴል ፈተና ወስደው ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑም እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
መ/ር ቶማስ አወቀ፣ የኪነ – ህንፃ ትምህርት ክፍል ኃላፊ በበኩላቸው፤ የትምህርት ክፍላቸው ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንደሚፈተኑ ገልጸው፤ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ብሉፕሪንት መሰረት አስፈላጊ ዝግጅት በማድረግ የቅድመ መውጫ ፈተና እንዲፈተኑና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት እንዲያዳብሩ መደረጉን ገልጸውልናል።
መ/ር በቀለ አሰፋ፣ የሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ምህድስና ትምህርት ክፍል ኃላፊ፤ ባለፈው ዓመት በተሰጠው የመውጫ ፈተና ትምህርት ክፍላቸው ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በዘንድሮ የመውጫ ፈተናም አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የባለፈውን ጥሩ ተሞክሮ በማጠናከር አንደኛው ዙር የተመራቂ ተማሪዎች ቅድመ መውጫ የሙከራ ፈተና መሰጠቱን አስገንዝበዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት