Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፣ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት የተሻሻሉና ምርታማነታቸው በምርምር የተፈተሸ የእንሰት ዝርያዎችን ስርጭት አካሂዷል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ም/ኘሬዝዳንትና የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ተወካይ ደረጄ አንዱዓለም (ዶ/ር)፤ አርሶ አደሩ በማሳው የሚተክላቸው የእንሰት ዝርያዎች በውስን ቦታ በቂ ምርት የሚሰጡ መሆኑን ገልፀው፤ ለአርሶ አደሩ የተሰራጩት የእንሰት ዝርያዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ገቢውን ለማሳደግ ብሎም ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ እንደሆነ ገልጸዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ እንሰት ለቡና ምርታማነትም ሆነ ለመሬት ለምነት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና ድርቅን በመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ተክል መሆኑን አንስተው ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን ገልጸዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ በበኩላቸው፤ ለዚህ ውጤት የበቃነው በዩኒቨርሲቲው ምሁራን እና በወረዳው ቀና ትብብር መሆኑን አንስተው፤ ይህንን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የይርጋጨፌ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ጅግሶ፤ ወረዳው በቡና እና በእንስት ምርት የሚታወቅ መሆኑን አንስተው፤ ዩኒቨርሲቲው በምርምር የተሻሻለ ምርት የሚያሰጥና የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ብሎም ገቢውን ከፍ ለማድረግ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሆልቲካልቸር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ መምህር ጨምር ጨዋቃ፣ በዱማርሶ የችግኝ ጣቢያ የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች በወረዳው ለአራት ቀበሌያት ለእያንዳዱ ቀበሌ 16 አርሶ አደሮች በድምሩ 64 አርሶ አደሮች እያንዳዳቸው 35 የእንሰት ችግኞች እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች 225 የእንሰት ችግኞች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።
የተሻሻለ የእንሰት ዝርያ ከተረከቡት መካከል አቶ ስለሽ ጠቀቦ ከቆንጋ፣ እንዲሁም ወ/ሮ አበራሽ ነጋሽ ከዶማርሶ፣ በምርምር የለሙ የእንሰት ችግኞችን ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረው ዩኒቨርሲቲው የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ እያደረገ ያለውን እገዛ ማድነቃቸውን ገልጸውልናል።
በቀጣይም በሌሎች የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላት የተሻሻሉ እና ውጤታማነታቸው በምርምር የተረጋገጡ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች እንደሚሰራጩ ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *