Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርማቲክስ ት/ቤት በቴክኖሎጂ ዙሪያ ሴሚናር ባዘጋጀበት ወቅት በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ተሰርቶ የቀረበው ተማሪዎችን ሊያግዝ የሚችል “Virtual Assitance (chatbot )” በትምህርት ክፍሉ እውቅናን አግኝቷል።

በዩኒቨርሲቲው የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህር እና የኮምፒዩቲንግና ኢንፎርማቲክስ ት/ቤት ዲን የሆኑት መ/ር ነጋ ተፈራ፣ የኮምፒተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ከዚህ የትምህርት ዘመን ጀምሮ የትምህርት ክፍሉን መምህራን እና ተማሪዎችን በማሳተፍ በየ15 ቀኑ የቴክኖሎጂ ሴሚናር እያዘጋጀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መ/ር ነጋ አክለውም፤ በትምህርት ክፍል ደረጃ የሚዘጋጀው ሴሚናር በዋናነት ስለ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ውይይት የሚደረግበት እንደሆነና በተጨማሪም የተሰሩ ስራዎች እንዲወጡ መስመር የሚይዙበት፣ የተለያዩ የምርምርና የስርፀት ሀሳቦች ለተማሪዎች እና መምህራን ለውይይት ቀርበው በሐሳቦች መነሻነት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እስከ መስራት የሚያደርስ መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል። አያይዘውም፤ በቀጣይ ከዚህ ሰፋ ባለ መልኩ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሴሚናሩ ከዩኒቨርስቲ ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ ጠቃሚ የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚቀርቡበት በመሆኑ በስፋት ተደራሽ ይሆን ዘንድ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አንስተዋል።

መ/ር ነጋ አያይዘውም፤ በዚህኛው ዙር የሴሜናር መድረክ በይበልጥ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በተለያዩ ትምህርቶች እና ርዕሶች ዙሪያ ለማንበብና ጥያቄዎችን ለመለማመድ የሚረዳ መተግበሪያ (Application) በትምህርት ክፍሉ የ3ኛ ዓመት ተማሪ ተሰርቶ ቀርቦ በቀረበው መተግበሪያ ዙሪያ ውይይት ተደርጎ እንዲሁም የማስተዋወቅ እና እውቅና የመስጠት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

መተግበሪያውን (Application) ያቀረበው የኮምፒተር ሳይንስ የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ተማሪ ናትናኤል ስንታየሁ በበኩሉ፤ አሁን ላይ አዲስ ያበለጸጋቸው መተግበሪዎች ሦስት ቢሆኑም ለዛሬው ሴሚናር “du chat bot” መተግበሪያን እንዳቀረበ ገልጾ፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ስለ ተቀሩት ሁለት ተጨማሪ ስራዎቹ የግንዛቤ ገለጻ አድርጓል።

ተማሪው ስለ መተግበሪያው ሲያስረዳ፤ ይህ መተግበሪያ ተማሪዎች ማንኛውንም መረጃ በሚፈልጉበት ወቅት “Chat bot” ውስጥ በመግባት ብቻ ጥያቄ አቅርበው የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ እንደሚያስችላቸው ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ በረዣዥም አንቀጽ ተጽፈው በቀላሉ መረዳት የሚከብዱ ሃሳቦችን መተግበሪያው በአጭሩ እንዲጽፍላቸው ቢፈልጉ ርዕሱን ብቻ በመጻፍ ጽሁፉን በአጭር አንቀጽ ተቀንብቦ ማግኘት እንደሚችሉ ተናግሯል።

ይህም ጊዜን ከመቆጠብ አንጻር ለተማሪዎች የሚያስገኘው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጾ፤ የቴክኖሎጂ ሴሜናሩ በየ15 ቀኑ መካሄዱ ተማሪዎች በዘርፉ የተለያዩ አዳዲስ ሶፍትዌሮችና መተግበሪያዎችን ማበልጸግ እንዲችሉ ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር እንደሆነ ተናግሯል።

ይህ ሴሚናር እንዲህ ያሉ በትምህርት ክፍሉ መምህራን እና የተለያዩ ተማሪዎች እየተሰሩ የሚቀርቡ አዳዲስ መተግበሪያዎች መሬት ወርደው የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ሴሜናር እንደሆነ ከአዘጋጆቹ ተገልጿል።