Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ ነሐሴ 20/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከቡሌና ራጴ ወረዳ ለተወጣጡ አርሶ አደሮች በምርምር የበለፀገ የአኘል ችግኝ ስርጭት አካሂዷል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ ዩኒቨርሲቲው በደጋ ፍራፍሬ ዙሪያ በሰፊው እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በዋናነት በአኘል ላይ ለረጅም ጊዜ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ከቡሌ ወረዳ 8 ቀበሌዎች ከራጴ ወረዳ በተመሳሳይ 8 ቀበሌዎች ለተወጣጡ አርሶ አደሮች የአኘል ችግኝ መሰራጨቱን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም፤ የአኘል ችግኝ ባለፉት ጊዜያት ከጨንቻ እያስመጡ ለአርሶ አደሮች ያሰራጩ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው በራሱ ባለሙያዎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የአኘል ችግኝ በማዘጋጀት እያሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ንጉሱ ደበበ፣ የዩኒቨርሲቲው መምህርና የአፕል ፕሮጀክት ተመራማሪ በበኩላቸው፣ የምርምር ማዕከሉ በዛሬው እለት ከሁለት ወረዳዎች ለተወጣጡ 160 አርሶ አደሮች ለእያንዳንዳቸው 25 ችግኞችን፤ በአጠቃላይ 4ሺህ የአኘል ችግኞች ለስርጭት ማብቃቱን አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ ሀይሌ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የማህበረሰብ ጉድኝትና አረንጓዴ ልማት ኦፊሰር፤ በደጋው አካባቢ ምርታማነታቸው የተረጋገጡ ስድስት የአፕል ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መሆናቸውን ገልፀው፤ አኘል ዛሬ ላይ የአርሶ አደሮችን የኑሮ ደረጃ እያሻሻለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የአኘል ችግኝ ስርጭት ከተቀበሉት መካከል አቶ ሀይሉ አባይነህና ወ/ሮ ፍሬነሽ ሽብሩ፤ የአፕል ችግኝ በማግኘታቸው ደስ መሰኘታቸውን ገልጸውልናል።

ዲላ፤

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et

Telegram:https://t.me/dprd9

website: https://www.du.edu.et

Email: https://www.pirdir@du.edu.et