Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 3 እስከ 11 በወረቀት እና በበይነ መረብ በሁለት ዙሮች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ፤ ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም አቶ ሙሉዓለም መኮንን ፣ በፈተናው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ማዕከል ኃላፊ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ችሮታው አየለ በመግለጫቸው፤ በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 3 ጀምሮ በሁለት ዙር በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካለምንም የጸጥታ ችግር ፍጹም ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ለዚህም ባለፉት ጊዜያት ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን እንደ ተቋም አስቀድሞ ከግንዛቤ በማስገባት እና ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ከፀጥታ አካላት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከፈተና ማዕከል ኃላፊዎች፣ ቺፎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞችና ሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ አመርቂ ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።
ዶ/ር ችሮታው አክለውም ፤በዚህ አመት በልዩ ሁኔታ የፈተና አሰጣጡ ተለውጦ ከወረቀት ባለፈ በኦንላይን ጭምር የተጀመረ በመሆኑ እንደ ዩኒቨርሲቲ የተወሰኑ ተማሪዎችን በበይነ መረብ ማስፈተን መቻሉን ተናግረው በቀጣይ ወደዚህ ሲስተም ለመግባት እንደ ሀገር ጭምር አቅጣጫ የተቀመጠ ስለሆነ በመጪው አመት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ የበይነ መረብ ተፈታኞችን ለመፈተን እንደ ተቋም ከወዲሁ ዝግጅት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ዶ/ር ችሮታው አያይዘውም፤ ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ፤ የፈተና ግብረ ሀይሉን ጨምሮ የፀጥታ ዘርፍ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር፣ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች እንዲሁም የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከሙሉ አባላቱ ጋር ሆነው ተማሪዎችን በመቀበል፣ ለተማሪዎች ሰዓት በማሳወቅ፣ ቅስቀሳዎችን በማድረግና በመሸኘት ጭምር ርብርብ በማድረጋቸው ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸው አቅርበዋል።
አቶ ሙሉዓለም መኮንን ፣ በሀገር አቀፍ ፈተና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ማዕከል ኃላፊ በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው በሁለት ዙር በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው ፈተና ያለምንም ችግር በታቀደለት ጊዜ እና በሚፈለገው ልክ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸው ፤ ለዚህም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የፀጥታ አካላት እና የፈተና አስፈጻሚዎች ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለዳረጉት ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን ብለዋል።
በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው ቆይታ ከአቀባበል ጀምሮ ለተደገላቸው መልካም መስተንግዶ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው ፤ የጸጥታ አካላቱ ፈተና ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ የአካባቢውን ደህንነት ለ24 ሰዓት በንቃት በመጠበቅ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተጫወቱት ትልቅ ሚና ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በዚህኛው ዙር ፈተናቸውን አጠናቀው ሲወጡ ያነጋገረናቸው ተፈታኞች ተማሪ መልካሙ በቀለ እና ተማሪ ሊድያ አብርሃም በበኩላቸው፤ ፈተናው በሰላም መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፤ በዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል እና ለነበራቸው ቆይታ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከዲላ ከተማ አቅራቢያ ከተሞች የመጡ ተፈታኞች ዛሬ ማምሻውን ወደየመጡበት ሲመለሱ የተቀሩት ከሱማሌ ክልል ፣ ከጌዴኦ ዞን እና ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ አካባቢ የመጡ ተፈታኞች በነገው እለት እንደሚሸኙ እና ለዛም የየትምህርት መምሪያ ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎች ተገቢውን ትራንስፖርት አዘጋጅተው እየጠበቁ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et