Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 22/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ም)፦ በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና የመምህራን የስልጠና አጀማመር ገለፀ (Orientation) ተሰጥቷል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የተጀመረውን የትምህርት አጠቃላይ ሪፎርም ለማሳካት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ጠቁመው፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ በመስጠት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጅቶችን አጠናቆ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ይህን የማስጀመሪያ መርሐግብር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ማከናወኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኞች የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው መልካምና ውጤታማ እንዲሆንላቸው ፕሬዝዳንቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ትምህርት በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራና በቂ ልምድ ያለው መሆኑንን አውስተው፤ በአሁኑ ስልጠና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተውጣጡ 505 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ከትምህርት ሚኒስቴር በዲላ ዩኒቨርሲቲ መመደባቸውን ተናግረዋል።
አቶ ገብሬ ነጋሽ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በዚህ ዙር 52 ሺህ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና 8 ሺህ የትምህርት ቤት አመራሮች በአጠቃላይ 60 ሺህ ሰልጣኞች በ28 ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና እንደሚወስዱ ጠቅሰው፤ መምህራን ለ120 ሰዓት በተማሩበት ሙያ፣ በትምህርት ስነዘዴ በሶሻል ሳይኮሎጂና ዲጂታላይዜሽን እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራሮች ለ60 ሰዓት በትምህርት አመራር፣ በሶሻል ሳይኮሎጂና ዲጂታላይዜሽን ስልጠና ወስደው በተከታታይ ምዘና 30 ከመቶ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር በሚዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ ውጤት ተይዞላቸው በድምሩ 70 ከመቶና ከዛ በላይ ውጤት ለሚያመጡት ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት እንደሚሰጣቸው አቶ ገብሬ አስገንዝበዋል።
በመርሐ ግብሩ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር፤ ለሰልጣኞች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et