Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፣ ጥር 10/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች የህፃናት ድንገተኛ ህክምናን፣ የጨቅላ ህፃናት እንክብካቤን እና የምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናት የህክምና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ተካልኝ አያሌው፣ በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል የይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን አቅም ለማጎልበትና ያለውን ችግር በመለየት፣ አብሮ ለመስራት በተቀመጠው አቅጣጫ ለህክምና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመደረጉ አመስግነዋል።
በዚህም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በመላክ በሳምንት ሁለት ጊዜ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ የአከባቢው ማህበረሰብ በከፍተኛ ህክምና ፍላጎት ሳይጉላላ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ እየተደረገ እንደሆነና ከዚህ በፊት ሲሰራ ያልነበረ የቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት መሰጠት መቻሉን ገልጸዋል። አያይዘውም፤ በህፃናት ድንገተኛ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች ለህጻናት ተገቢው አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ፤ በጤናው ዘርፍ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ አንስተው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የተቋሙ የትኩረት አቅጣጫ አንዱ በሆነው የጤና ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን አድንቀው ሰልጣኞች በበኩላቸው ለጤና ጣቢያዎች እና ለጤና ኬላዎች ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር እንየው መለሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል የህፃናት እስፔሻሊስት ሐኪም እንዲሁም ዶ/ር ሀዊ መሐመድ የህፃናት ድንገተኛ ክፍል ሐኪም፤ በጨቅላ ሕፃናት እንክብካቤ እና የምግብ እጥረት ባለባቸው ሕጻናት ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙዎችን ለማብቃት የተሰጠ ስልጠና መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ሰልጣኞች ባገኙት እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው ህሙማን በማገዝ ላይ አመርቂ የሆነ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይነት የተለያዩ አስፈላጊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ትዝአለኝ ፤የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለመጨመርም ሆነ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸው የአቅም ግንባታ ስልጠናው እንዲሳካ በማድረጉ የይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማኔጅመንትን በማመስገን ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ህብረተሰብን ለማገልገል እንዲያውሉት አሳስበዋል።
ከሰልጣኞች መካከል የጨቅላ ህፃናት ክፍል ነርስ የሆኑት ሲስተር ብርአለም አብዲ እና ክሊኒካል ነርስ ረድኤት ብርሃኑ ከስልጠናው የተሻላ እውቀት እንደቀሰሙ ገልፀው፤ ይህን መሰል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ለሌሎችም ባለሙያዎች ቢሰጡ ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚያግዙ ገልጸውልናል።
በአቅም ማጎልበቻ ስልጠናው ከሆስፒታሉ በድንገተኛ ክፍል፣ በጨቅላ ህፃናት ክፍል እና በምግብ እጥረት ክፍል የሚሰሩ 15 ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት