Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በጌዴኦ ዞን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ (Online) ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ይረዳል የተባለ የሞዴል ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል።
አቶ ዘማች ክፍሌ፣ የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት መልኩ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጥ እንደመሆኑ መጠን ትምህርት ሚኒስቴር ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ከጌዴኦ ዞን በዩኒቨርሲቲው በቅርበት ያሉ እና በቴክኖሎጂው የተሻለ ልምድ ያላቸው ትምህርት ቤቶች ተለይተው ለፈተናው መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም እንደ ዞን ብሔራዊ ፈተናውን ከሚወስዱ አጠቃላይ 28 ትምህርት ቤቶች መካከል 3 ትምህርት ቤቶች ማለትም የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒቲ ት/ቤት፣ የዶንቦስኮ እና የዳማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተለይተው በአጠቃላይ 611 ተማሪዎችን በኦንላይን ለማስፈተን ዛሬ የሞዴል ፈተናውን በዲላ ዩኒቨርሲቲ መውሰድ መጀመራቸውን አቶ ዘማች ተናግረዋል።
እንደ አቶ ዘማች ገለጻ፣ የኦንላይን ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ስለፈተናው አጠቃላይ ጉዳዮች አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን ከሙከራ ፈተና በኃላ ደግሞ ስለፈተናው ሁኔታ በድጋሚ ተማሪዎችን የማወያየት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
አቶ በቀለ ወርቁ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አይ ሲ ቲ ዳይሬክተር፤ ከጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመነጋገር በኦንላይን ለሚፈተኑ ሶስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚሆኑ በቂ የሆኑ የኮምፒውተር ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው ዕለት የሞዴል ፈተናው በ8 የሙከራ ጣቢያዎች ላይ እየተሰጠ እንዳለ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም፤ እስካሁን ባለው ሂደት አብዛኛው ተማሪዎች ካለምንም እገዛ የመለያ ስም (username) እና የይለፍ ቃላቸውን (Password) በትክክል በመሙላት ሞዴል ፈተናውን በአግባቡ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት በጠዋቱ መርሃ ግብር በነበረው የሞዴል ፈተና ከሶስቱ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 187 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሞዴል ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን በከሰዓት መርሐ ግብር ደግሞ 85 የሚደርሱ ተማሪዎች በተመሳሳይ መልኩ የሚፈተኑ መሆኑ ተገልጿል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et