Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በጌዴ ዞን ለሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች በመሰረታዊ የቀዶ ህክምና ነርሲንግ አገልግሎት እና ኢንፌክሽን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ በላይ ዘውዴ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዞናችን ለሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች በተለይም በቀዶ ህክምና ክፍል ለሚሰሩ ነርሶች የሚሰጠው ስልጠና ዩኒቨርሲቲው በተለይም በዘንድሮ ዓመት በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ላይ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ በማሰብ እየሰራቸው ላሉት ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ባለሙያዎችን ከማብቃት እና እንዲሁም በቀዶ ህክምና አካባቢ ያሉ ስራዎችን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
አቶ ፈጠነ ባሌሲ፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የስልጠናና ማማከር ኦፊሰር፤ ስልጠናው ተግባር ተኮር ስልጠና እንደመሆኑ ለማህበረሰቡም ይሁን ለባለሙያው ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገለጸው፤ በተለይ ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኃላ ወደ ማህበረሰቡ ሲገቡ ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሁም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ከአሰልጣኞች መካከል በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር መኮንን ብርሃኔ በበኩላቸው፤ ለሁለት ቀናት በቆየው ስልጠና ለባለሙያዎቹ የተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ ባሉ አሰልጣኞች የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠቱን ገልጸው፤ ከእነዚህም ውስጥ በሳቸው የተሰጠው ከተላላፊ በሽታዎች አንፃር ሰዎች ለህክምና ወደ ጤና ተቋማት ሲመጡ በሽታዎችን ታክመው ሲወጡ ሌላ ተላላፊ በሽታዎችን ይዘው እንዳይሄዱ እና እነሱም ደግሞ ወደ ጤና ተቋማት ሲመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ይዘው እንዳይመጡ ለመከላከል የተሰጠ እንደነበር ተናግረዋል።
በስልጠናው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ ይህ ስልጠና ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ላይ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ሌሎች በዞኑ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችም ተመሳሳይ ችግሮች ስለሚስተዋልባቸው ባለሙያዎች በአንድነት ስልጠና ቢያገኙ ከሚሉ ሃሳቦች መነሻነት ስምምነት ላይ ተደርሶ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ አስረድተዋል።
ስልጠናውን ሲሳተፉ ያገኘናቸው ከይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጡት ሲስተር ቤተልሄም ገብሬ እንዲሁም ከቡሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጡት አቶ ታደለ ማርያም፤ ስልጠናው ተግባር ተኮር ስልጠና እንደመሆኑ ብዙ እውቀትን ያገኙበት እንደነበር ገልጸው፤ በቀጣይ እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች በሰፊው ብዙዎችን አሳታፊ ባደረገ መልኩ ቢሰጥ በጤና ተቋማት ላይም ሆነ በባለሙያው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስተያየት ሰጥተዋል።
በስልጠናው በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ሦስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ማለትም ከይርጋጨፌ፣ ከቡሌ እና ገደብ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የተውጣጡ 36 የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et