ለዲላ ዩኒቨርሲቲ እና አካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት ኤጀንሲ እና ከደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር
“መጻሕፍት ለእውቀት ገበታ፤ መዛግብትና የጽሁፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ”
በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 12-16/2014 ዓ.ም የሚከበር የንባብ ሳምንት፣ የቡክፌር፣ የኤግዚብሽን እና የፓናል ውይይት ፕሮግራም በዲላ ከተማ አዘጋጅቷል፡፡
‹ፕሮግራሙ›
ቅዳሜ ማለትም የካቲት 12/14 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በማዞሪያ አደባባይ በተዘጋጀው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ በተማሪዎች የሰልፍ ትርዒት ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የባህል ኪነት ቡድን የተለያዩ ሙዚቃዎች፣ ሰርከሶች ይቀርባሉ፤ ስለ ንባብ አስፈላጊነትም የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡
ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመጽሐፍት ሽያጭ ባዛር የተዘጋጀ ሲሆን እስከ 50% ቅናሽ ባለው ዋጋ የተለያዩ መፅሐፍቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ
ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ዮሐንስ ገ/መድህን፣ ደራሲ ገዛኸኝ ሀብቴ እና ሌሎችም ታዋቂ የጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት የኪነ-ጥበብ ፕሮግራም ይቀርባል
በዲላ ከተማ የሚገኙ ት/ት ቤቶች ይጎበኛሉ፣ የንባብ ክበባትም ይመሰረታሉ
በንባብ ባህል እና በቤተ መዛግብት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፓናል ዉይይት ይካሄዳል
ለተለያዩ ት/ት ቤቶች እና የህዝብ ቤተ መፃህፍቶች ነፃ የመፅሐፍት ድጋፍ ይደረጋል
በመሆኑም የከተማችን ማህበረሰብ በሙሉ የመፅሐፍት ሽያጭ ባዘሩን በመጎብኘት እስከ 50% ቅናሽ ባለው ዋጋ የቀረቡ መጽሐፍትን ለራሱ፤ ለልጆቹ እና ለወዳጆቹ ይገዛ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዟል፡፡
የከተማችን በጎ ፈቃደኛ ሰዎችም አንድ መፅሐፍ ለአንድ አንባቢ በሚል መርህ መፅሐፍት ገዝተው ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡ በኪነ-ጥበብ ፕሮግራም እና በፓናል ዉይይት ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ የተላለፈላችሁ እንግዶቻችንም ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
“መጻሕፍት ለእውቀት ገበታ፤ መዛግብትና የጽሁፍ ቅርሶች ለዘመን ትውስታ”
...................
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት ኤጀንሲ
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ