Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

በሰላም እሴቶች ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

በሰላም እሴቶች ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

በቡና ጥራት ቅምሻ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

በቡና ጥራት ቅምሻ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 11/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በአቶ ተካልኝ ገሎ የተመራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ቡድን የዲላ ዩኒቨርሲቲ “STEM” ማዕከልን ጎብኝቷል።
ችሮታው አየለ (ደ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለልኡካን ቡድን አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጋር በአገር ልማትና እድገት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአይሲቲ ልማት፣ በችግር ፈቺ ፈጠራዎችና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት ተቋማችን ዝግጁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ተካልኝ ገሎ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ “STEM” ማዕከል በማደራጀት የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመቀበል ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሥራ ማመንጨት እንዲችሉ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርት በመስጠት ተማሪዎች አመርቂ ስራዎችን እንዲሰሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ተካልኝ አያይዘውም፤ በጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቷቸው የፈጠራ ውጤቶች ወደ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ተቀይረው ለባለፈጠራዎቹ የድካማቸውን ዋጋ የሚያገኙበት እንዲሁም ለአካባቢው ማሕበረሰብ ችግሩን የሚፈታበት እንዲሆን ቢሯቸው ከዲላ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት፣ በጉብኝቱ መርሀ ግብር ባሰሙት ንግግር፤ “STEM” ማዕከል የሚማሩ ተማሪዎች በየዓመቱ እንደሚመረቁና የራሳቸውን ችግር ፈቺ ፈጠራ ሥራ ሰርተው በሚዘጋጀው አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙና ይህ ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብሎም ፍሬ እንዲያፈራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በአጋርነት እንዲሰራ ጠይቀዋል።
አቶ ተስፋጽዮን ዳካ፣ የጌዴኦ ዞን መንግሥት ረዳት ተጠሪ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ፈጠራ እውቀት ለማስፋት “STEM” ማዕከል በማደራጀት በጌዴኦ ዞንና አጎራባች ክልል ወረዳዎች ተማሪዎችን በማስተማር አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ አመላክተው፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊና ማኔጅመንት አባላት ያደረጉት ጉብኝት አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ተናግረዋል። ማዕከሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ተስፋጽዮን አያይዘው ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ወቅት በማዕከሉ ከተሰሩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎች ለጎብኝዎች ቀርበው ገለጻ ተደርጎባቸዋል።
በጉብኝት መርሃ ግብር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የበላይ አመራሮች፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አመራሮች፣ የጌዴኦ ዞን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አመራሮች፣ የማዕከሉ መምህራን፣ ተማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin