ለዲላ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

ማስታወቂያ(የታረመ)
ለዲላ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

እንኳን ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለን
1. አጠቃላይና ነባር የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያና የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 21 እና 22 ቀን 2012 ሲሆን የመጨረሻ በቅጣት ምዝገባ የሚፈጸመው መስከረም 23፣2012 ብቻ ይሆናል፡፡
2. አዲስ አንደኛ ዓመት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያና የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ሲሆን የመጨረሻ በቅጣት ምዝገባ የሚፈጸመው መስከረም 28፣2012 ዓ.ም ብቻ ይሆናል፡፡
- በተጠቀሱ ቀናት ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ስርተፊኬት፣ ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል መሰረተ ትምህርት የአጭር ጊዜ ስልጠና እየተሰጠ ነው

ዲዩ፤ ነሐሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ከኮምፒውቲንግ እና እንፎርማቲክስ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ሁለት ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የኮምፒውተር መሠረታዊ ዕውቀት(Computer Basics)፣ የበይነ መረብ አገልግሎቶች አጠቃቀም (The Internet, cloud services and world wide web)፣ የአገልግሎት ሰጪ መተግበሪያ ፕሮግራሞች አጠቃቀም(Productivity Programmes)፣ የዲጂታል አኗኗር (Digital lifestyles)፣ የግል መረጃ ደህንነት አጠባበቅ(Computer security and privacy) በዲጂታል መሠረተ ትምህርት (Digital Literacy) ስልጠና እየተዳሰሱ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡

Announcement

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በወጣው የምክትል ፕሬዚዳንት ከፍት የሥራ ቦታዎች ለመወዳደር ላመለከታችሁ ተወዳዳሪዎች ጳጉሜ 1/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ በመገኘት የተቋሙን አንኳር ተግባራትን ለማሳካት ያዘጋጃችሁትን ዕቅድ ስለምታቀርቡ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአረንጓዴ አሻራ ቀን

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአረንጓዴ አሻራ ቀን ከ10 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች ተተከሉ
ዲዩ፤ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የአረንጓዴ ቀንን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ የዕፅዋት ጥበቃና ኢኮ-ቱሪዝም ማዕከል ችግኝ ተከለዋል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በታሪካዊው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የተቋሙ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ተማሪዎች በነቂስ ወጥተው በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል፡፡
በተያዘው ዓመት ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት በመስጠት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ጥሪ ሁሉንም ያነቃና አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ተናግረዋል፡፡
የበረሀማነት መስፋፋትን ለመግታትና ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መሠጠቱ አስፈላጊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማኅበረሰቡ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ባህል ማዳበር ይኖርበታል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ማስታወቂያ

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በዲላ ዩንቨርሲቲ ለ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በ “Natural Resources Management for Sustainable Agriculture” የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሰው ቀን የትምህርት ማስረጃችሁን እና የምርምር ንድፈ ሀሳባችሁን (research concept note) በመያዝ የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የድህረ ምረቃ ት/ቤት ቢሮ እንድትገኙ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
 0911967032
 046331122

መደወል ይችላሉ