ዲ.ዩ፤ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማፍጠን የልየተና የትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ተቋቁሞ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር የተቋቋመው ይህ ዳይሬክቶሬት ዩኒቨርሲቲው ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገውን ሽግግር በአግባቡ እንዲመራና አዳዲስ መመሪያዎችን እንዲያዘጋጅ፣ የነበሩትን ወደ መሬት ማውረድ እንዲቻል ታስቦ የተቋቋሙ ክፍል ነው ብለዋል፡፡
የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮው ተግባር ተኮር ትምህርት መስጠት መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህ የሚረዳ ስርዓተ ትምህርት እንደ አዲስ ክለሳ እንደሚደረግና ያልተሟሉ ነገሮች ተሟልተው ተማሪዎች በቤተ-ሙከራ እንዲሁም በኢንዱስትሪ በቂ ልምምድ አግኝተው እንዲወጡ ከዩኒቨርሲቲው እንደሚጠበቅ ዶ/ር ጌታነህ አያይዘው ገልጸዋል።
የልየታና የትኩረት መስክ ም/ዳይሬክተር አብዱ ሀሰን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዚህ ልየታና የትኩረት መስክ ስራ በዋናነት ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው የትኩረት መስክ በብቃት እንዲወጡና የአካባቢያቸውን ጸጋ ባገናዘበ መልኩ እንዲሰሩ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

